የሀገር ውስጥ ዜና

የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊት አባላት ድጋፍ አደረጉ

By Feven Bishaw

November 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊት አባላት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ ።

በቢሾፍቱ የመከላከያ ኮምፕሪሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በመከላከያ ዋር ኮሌጅ በመገኘት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ ያስረከቡት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ እንዲሁም የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ናቸው።