የሀገር ውስጥ ዜና

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል

By Alemayehu Geremew

November 12, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በቲቺንግ ሆስፒታል ግቢ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሠለጠናቸውን ከ400 በላይ ተማሪዎችን በነገው ዕለት ያስመርቃል፡፡

በነገው ዕለት የሚመረቁ ተማሪዎች በአምስት የትምህርት ዘርፎች የሰለጠኑ መሆናቸውን የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ሄኖክ ገልፀዋል፡፡

በምረቃ ፕሮግራሙ ከሣይንሥና ከፍተኛ  ትምህርትተቋማት እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተስፋዬ ምሬሳ