የሀገር ውስጥ ዜና

የፍትህ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

By Feven Bishaw

November 12, 2021

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በህልውና ዘመቻው ለተጎዱ ወገኖች ደም ለግሰዋል፡፡

ደም የመለገስ መርሃ ግብሩ የህልዉና ዘመቻዉ ከተጀመረ የአሁኑ ለ3ተኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን÷ በፍትህ ሚኒስቴር የመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አለም አንተ አግደዉ በአሁኑ ወቅት የዉስጥና የዉጭ ሀይሎች በአገራችን የደቀኑትን አደጋ ተከትሎ መንግስት ያቀረበዉን ጥሪ በመቀበል ዜጎች በእልህና በወኔ ተንቀሳቅሰዋል ብለዋል፡፡