ሠራዊቱ በተሳካ ሁኔታ ግዳጁን እየፈጸመ ይገኛል- ብ/ጄ ተስፋዬ ረጋሳ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ግንባር የተሰለፈው የአገር መከላከያ ሰራዊት ግዳጁን በተሳካ ሁኔታ እየፈጸመና በጠላት ላይ ድል እየተቀዳጀ መሆኑን ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ረጋሳ ገለጹ።
በወሎ ግንባር ከሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አዛዞች አንዱ የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ እንደሚሉት፥ ሠራዊቱ አሁን ላይ የተሳካ የግዳጅ አፈጸጸም ላይ ይገኛል።
አዛዡ አክለውም ሠራዊቱ አገሩን እያሰበ በእልህና በወኔ፥ ለህዝብና ለአገር ሰላም እና መረጋጋት ከጠላት ጋር እየተፋለመ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የሰራዊቱ የግዳጅ አፈጻጸም ስኬታማ ነው ያሉት አዛዡ፥ “ስለ ድሉ እኛ ከምናወራው ይልቅ የሠራዊቱ የጦር ሜዳ ውሎ እና የጁንታው ምርኮኞችን ምስክርነት መስማት በቂ ነው” ብለዋል።
የህዝቡ ደጀንነት ከቃላት በላይ ነው ሲሉ የገለጹት አዛዡ፥ በተለይም ጦርነቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ያለው ህብረተሰብ ከልጅ እስከ አዋቂ ግንባር ድረስ በመምጣት አጋርነት እያሳየ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ሠራዊቱ ከህዝቡ የተቀበለውን አደራ ሳያጓድል ጁንታውን አአስወግዶ የህዝቡን ፍላጎት ያሳካል፤ ለዚህ ደግሞ ህዝቡ ቅንጣት ታክል ሊጠራጠር አይገባም ነው ያሉት ጀኔራል መኮንኑ።
“ከህዝቡ የተቀበልነውን አደራ እናሳካለን” ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ፥ ጁንታው የወገንን መሬት ዳግሞ እንደማይረጋጥ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሠራዊታችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የጁንታውን ወራሪ ሃይል ደምስሶ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ያረጋግጣልም ነው ያሉት።
በብስራት መንግስቱና በምናለ ብርሃኑ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን