የሼህ ሰኢድ ሁሴን የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ሱመያ መስጅድ ለረጅም አመታት ኢማም ሆነው ያገለገሉት እና ታላቅ የሃይማኖት አባት የሆኑት የሼህ ሰኢድ ሁሴን የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ።
ሼህ ሰኢድ በሆስፒታል ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው፥ በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የታላቁ አሊም ሼህ ሰኢድ ሁሴን ስርዓተ ቀብርም በርካታ ኡለማዎች ፣ ዱአቶች እና ምዕመናን በተገኙበት ዛሬ በኮተቤ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈጽሟል ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ ” ታላቁ አሊም ሼህ ሁሴን ትውልድን በእውቀት እና በስነ ምግባር ያነጹ የአገር ባለውለታ የእስልምና ሊቃውንት ነበሩ ” ብለዋል።
ሼህ ሰኢድ ለእስልምና ካበረከቱት አስተዋጽኦ ባሻገር በሃገር ሽማግሌነታቸው፣ ለሃቅ የቆሙ እና በአስታራቂነታቸው የሚታወቁ እንደነበሩም ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ ተናግረዋል።
በአወል አበራ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን