የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና አልማ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

By Feven Bishaw

November 12, 2021

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሽብርተኛው ህወሓት ምክንያት ከወሎ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች የ3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ የየካ ክፍለ ከተማ የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ሀብት በማሰባሰብ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብና ቁሳቁስ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡