የዞኑ ህዝብ ለህልውና ዘመቻ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ህዳር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የምስራቅ ሸዋ ዞን ህዝብ መንግስት በቅርቡ ያቀረበውን የክተት ጥሪውን በመቀበል ለህልውና ዘመቻው በጥሬ ገንዘብ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ብርና ሌሎች የአይነት ድጋፍ ማድረጉን አስተዳዳሩ አስታወቀ።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ ለኢዜአ እንደገለጹት መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ሀገር ለማዳን ውድ ህይታቸውን እየገበሩ ይገኛሉ።
የዞኑ ህዝብ ከዚህ ቀደም በህልውና ዘመቻው እየተሳተፉ ላሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ ሀይሎች በገንዘብና በአይነት ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።
አሁንም መንግስት በቅርቡ ያቀረበውን የክተት ጥሪ በመቀበል ለሁለተኛ ጊዜ ለህልውና ዘመቻው በጥሬ ገንዘብ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም 67 ሰንጋዎች፣ 185 ፍየሎች እንዲሁም የደረቅ ስንቅ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል።
በጎ ፈቃደኛ ነዋሪዎችም 92 ዩኒት ደም መለገሳቸውን አመልክተዋል ።
የአሸባሪው ህወሀት ወራሪ ሀይል ሙሉ ለሙሉ እሰኪወገድ ህዝቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
ወጣቱ ሀገር አፍራሹን የህወሀት ሃይል ለመደምሰስ በቆራጥነት መነሳቱን የገለጹት አቶ አባቡ በዞኑ 4ሺህ 127 ወጣቶች በፍቃዳኝነት ወደ መከላከያና ሌሎች ልዩ ሀይሉን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።
“የክልሉን ልዩ ሃይልና መከላከያን በሰው ሃይል ለማጠናከር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።
የዞኑ ሚሊሻ አባላትም ሀገር ለማመስና ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳውን አሸባሪውን ሕወሀት እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን