የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የተሰበሰበውን የገንዘብ እና የአይነት ድጋፉን ተረክበው ለመከላከያ ሰራዊት ተወካዮች አስረክበዋል ።
የኢትዮጵያ ልጆች አዲስ ድል እየተቀደጁ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአሸባሪውን የቅዠት ህልም እናጠፋዋለን ፤ ከፊት ሆነው የሚወጉን አሸባሪው የህወሓት እና ተላላኪው የውስጥ ባንዳዎች እንዲሁም በእጅ አዙር እየወጉን ያሉ የውጭ ሃይሎችን በጀግንነት እና በአንድነት ቆመን እንመክታቸዋለን ብለዋል ::
የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ዛሬ ያደረጋችሁት ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊታችን ሞራል ትልቅ በመሆኑ በቀጣይም አጠናክራችሁ መቀጠል ይኖርባችኋል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መላኬ አለማየሁ በበኩላቸው ዛሬ የተደረገው ድጋፍ ለ3ኛ ዙር መሆኑን ገልጸዋል።
ለመከላከያ ሠራዊቱና አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ወገኖች የተደረገው 170 ስንጋዎች ፣250 በግ እና ልዩ የምግብ አይነቶችን ጨምሮ በጠቅላላው ከ35 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ነው ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን