Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት አሁንም ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን በመጣስ ታዳጊዎችን ለጦርነት እያሰለፈ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት አሁንም ዓለም አቀፍ የህጻናት ድንጋጌዎችን በመጣስ ታዳጊ ህጻናትን ለጦርነት እያሰለፈ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ቡድኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ በተደጋጋሚ ታዳጊ ህጻናትን በጦርነቱ ሲማግድ ቆይቷል፥ አሁንም እየማገደ እንደሚገኝ በወሎ ግንባር የሚገኘው የኤፍ ቢ ሲ ጋዜጠኞች ቡድን አረጋግጧል።
ሰሞኑን በወሎ ግንባር ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን የሰጡ የአሸባሪው ቡድን ምርኮኞች ሁኔታ ይህን ያረጋግጣል።

ቡድኑ ቆሜለታለሁ ለሚለው ለትጋራይ ህብረተሰብ ሳይሆን የራሱን ጥቅምና ስልጣን ለማስበቅ በማሰብ የሚንቀሳቀስ መሆኑን ታዳጊ ምርኮኞቹ ተናግረዋል።

ታዳጊዎችን በግዴታ ወደ ግንባር ከማስገባቱም በተጨማሪ፥ በፕሮፓጋንዳና በጥላቻ ንግግር እንደሚሞላቸው ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን የሰጡ እነዚሁ ታዳጊ ምርኮኞች ይገልጻሉ።

ከምርኮኞቹ መካከል ከውቅሮ ማርያም እንደመጣች የምትናገረው ሰላም ጎራይዱላይ፥ በግዴታ ታፍሳ ግንባር መግባቷን ገልጻለች።
ከዚህ ቀደም ስለመከላከያ ሰራዊት መጥፎነት ሲነገራት እንደነበር ጠቅሳ፥ “መማረክ ባልፈልግም ሲደክመኝ እጀን ሰጠሁ” ትላለች።

ከባልደረባችን ጋር በነበራት ቆይታ እንደተናገረችው፥ “ቤተሰብ ለማትረፍ ብየ በግዴታ ነው የመጣሁት” ብላለች።
“ማይቅናጠል አንድ ወር ከሁለት ሳምንት ሰልጥነን የ3 ቀናት ጉዞ ካደረግን በኋላ ግንባር ገባን” የምትለው የ20 አመቷ ወጣት፥ በትውልድ አካባቢዋ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተማሪ እንደነበረች አስረድታለች።

“ከቤት ወደ ጦርነትት የሚሄድ ሰው ማዋጣት ግዴታ በመሆኑ እናት እና አባቴን ለማትረፍ ስል ወደ ግንባር ገብቻለሁ” ስትልም ትናገራለች።

ከእርሷ ጋር በርካታ ታዳጊ ወጣት ሴቶች ወደ ግንባር በግዳጅ መግባታቸውን የምትገልጸው ሰላም፥ ይህ እጣፋንታ ያልገጠማቸው የትግራይ ተወላጆች ካሉበት እንዳይወጡ መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

“ትግራይ ሳይሆን ኢትዮጵያ ተብሎ መጠራት ለስም እንኳን መልክ አለው” ስትልም የሽብር ቡድኑ የሄደበትን የክፋት ጥግ በቁጭት ኮንናለች።

ሌላኛዋ ምርኮኛና በግዴታ ወደ ግንባር የገባችው የ18 አመቷ ታዳጊ ኒያ ተወልደ፥ ከተንቤን መምጣቷን ትናገራለች።

ታዳጊዋ ከአንድ ወር ስልጠና በኋላ ከአቢይ አዲ ተነስተው ወደ ጦር ግንባር መግባታቸውንም ነው ያስረዳችው።

ታዳጊዋ ከአንድ ቤት አንድ ሰው ማዋጣት ግዴታ በመሆኑ በግዳጅ መግባቷንም ገልጻለች።

ከመማረኳ በፊት ስለመከላከያ ብዙ መጥፎ ነገሮች ትሰማ እንደነበር ጠቅሳ፥ እሷና ጓደኞቿ በምርኮኝነት ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በመከላከያ አስፈላጊው የምግብና ሌሎች አቅርቦቶች እየተደረገላቸው መሆኑን እና እንክብካቤ እንዳልተለያቸውም አስረድታለች።

ከብዘት አካባቢ እንደመጣች የምትናገረው ደግሞ ማህደር ሃዲሽ ናት።
እርሷም ከአንድ ቤተሰብ በግድ አንድ ልጅ አዋጡ በተባለው የግዴታ ኮታ መሰረት ከቤተሰቧ እሷ መውጣቷን ተናግራለች።

ማህደርም እንደ ሌሎች ጓደኞቿ የአንድ ወር ስልጠና ወስዳ ወደ ግንባር መግባቷን እና በወሎ ግንባር አካባቢ ለመከላከያ እጅ መስጠቷን ነው የገለጸችው።

አዲስ አበባ ልንገባ ነው ፣ ስናሸንፍ ስራ እንሰጣቸኋለን ፣ ካልዘመታችሁ ለቤተሰቦቻችሁ የእርዳታ እህል አንሰጥም በሚል ማስፈራሪያ ወደ ግንባር እንዳስገቧቸውም ምርኮኞቹ ይናገራሉ።

ከተማረኩ የሽብር ቡድኑ አባላት መካከል እድሜያቸው ለጦርነት ያልደረሱና የዓለም አቀፍ ህግን በጣሰ መልኩ ታዳጊ ህጻናት በግንባር ተሰልፈው በለጋ ዕድሜያቸው ህይወታቸውን እያጡ ነው ።

የታዳጊዎቹ ሁኔታ አሸባሪው ቡድን አሁንም ዓለም አቀፉን የህጻናት ድንጋጌ በመጣስ በጦር ወንጀለኝነት የሚያስከስሰውን ድርጊት እየፈጸም እንደሚገኝም ድርጊቱ የሚያሳይ ነው።

በብስራት መንግስቱና በምናለ ብርሃኑ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.