በዳውንት መስመር ቆርጦ ወደ ታች ጋይንት ለመግባት የሞከረው ጠላት ኪሣራ እየደረሰበት ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ይርጋ ሲሳይ በተለይ ለአሚኮ እንደገለጹት ጠላት ከሰሞኑ በዳውንት መስመር አድርጎ በታች ጋይንት ወረዳ በኩል ቆርጦ ለመግባት ሙከራ አድርጓል።
ይሁን እንጂ ሕዝቡንና የታጠቀውን ሃይል በማነቃነቅ የጠላትን እንቅስቃሴ መገደብ እንደተቻለና ጠላትም ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን ነው አቶ ይርጋ የተናገሩት።
የወገን ጥምር ጦር በቅንጅት ባካሄዱት ውጊያ ከፍተኛ ድል ማስመዝገባቸውን ጠቅሰው፥ በዚህም የወገን ጦር ገዢ ቦታዎችን መያዝ ችሏል ብለዋል።
የአካባቢውን መልክዓምድራዊ ምቹነት በመጠቀምና ከሌሎች ግንባሮች ጋር በመናበብ የሚጠበቅብንን እያደረግን ነው ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ ጥሩ ውጤት እየተገኘ እንደሆነ አመላክተዋል።
በውጊያው የታች ጋይንት ወረዳ ሕዝብ ደጀንነት በተለየ መልኩ ጠንካራ እንደሆነ በማንሳትም ወጣቶች እና አርሶ አደሩ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያደርገው ትብብር በግንባሩ የሚገኘው ውጤት በሚፈለገው መልኩ የተሳካ እንዲሆን አድርጎታልም ነው ያሉት።
የፖለቲካ መሪዎች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች መስዋዕትነት ለመክፈል ከፊት በመሰለፍ የማስተባበር፣ የማዋጋት፣ የመዋጋት እና የመምራት ሚናቸውን በአግባቡ እየተወጡ እንደሆነም ነው የገለጹት።
የህልውና ትግሉን ለሠራዊቱ ብቻ አንሰጥም ያሉት አስተዳዳሪው ጠላትን ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ መሪዎች እና ሕዝቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት እየተፋለሙ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
የስንቅና የትጥቅ አቅርቦቱም በተገቢ መልኩ እየቀረበ ነው ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን