Fana: At a Speed of Life!

ለፌዴራል መስሪያ ቤቶች ለኪራይ የሚወጣውን ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ለማስቀረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ለፌዴራል መስሪያ ቤቶች ዓመታዊ ኪራይ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣውን ወጪ ለማስቀረት ፕሮጀክት ቀርጾ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ጥቂት የማይባሉ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የራሳቸው ቢሮ የሌላቸው ከመሆኑ የተነሳ የመደበኛ ሥራዎቻቸውን ለማከናወን የማይመቹ፣ ለሥራ ተነሳሽነት የማያበረታቱና የማይማርኩ፣ ለተገልጋይ ደንበኛም ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የማይጋብዙ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በሌላ በኩል አገሪቱ ለሌሎች መሠረተ-ልማቶች ታውል የነበረውን ከፍተኛ መዋዕለ-ነዋይ ለኪራይ ወጪ በመዳረጉ ለአገራችን እድገት እንቅፋት እንደሆነ ማንም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በመንግስት ውሳኔ መሠረት የፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በሚል ስያሜ የተቋቋመ ተቋምን ዘርግቶ ዘመናዊና ጥራታቸውን የጠበቁ፣ በዋጋ ተደራሽ፣ በታቀደው ጊዜ ተጠናቀው ለሥራ ምቹ የሆኑ የሥራ አካባቢን መፍጠር እንዲቻል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብሏል፡፡
እስካሁን ተገንብተው ሥራ ላይ ከዋሉት መካከል የጤና ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የፌዴራል ስቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቢሮ፣ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ፣ የፌደራል መሬት ተቋማት ቢሮ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ቢሮ፣ የአገልግሎት ዘመናቸውን ላጠናቀቁ የመንግስትና የሀገር መሪዎች የመኖሪያ ቤት፣ የብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት፣ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የህንጻ ግንባታዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ከእነዚህ፣ ከላይ ከተዘረዘሩት ጥቅም ላይ ከዋሉት ህንጻዎች በተጨማሪ በርካታ የፌዴራል ህንጻዎች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
+3
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.