Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት ስልጣን በቃኝ የማይል ሴረኛ እና ጨካኝ ድርጅት ነው- የቀድሞ የኡጋንዳ አምባሳደር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሓት ተመልሶ ወደ ስልጣን መምጣት የሚፈልግ ሴረኛ እና ጨካኝ ድርጅት ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የቀድሞ የኡጋንዳ አምባሳደር ኤዲዝ ሴምፓላ ገለፁ፡፡
በኢትዮጵያ የነበራቸው ቆይታ አሸባሪው ህወሓት የችግሮች ሁሉ ምንጭ መሆኑን ለመረዳት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡
ከአገራቸው ጋዜጠኛ ኩንጉ አልመሃዲ አዳም ጋር ቆይታ ያደረጉት ኤዲዝ ሴምፓላ እንዳሉት፥ የህወሓት ቡድን ለመደገፍ ሲሉ የምዕራቡ ዓለም ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚያናፍሱት የውሸት ወሬ የአፍሪካን ጋዜጠኞች የሚያነቃ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በአካል ባላውቃቸውም፥ ሰላምንና ፍቅርን ተቀዳሚ ተግባራቸው ያደረጉና በህዝብ ይሁንታ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሪ ናቸው ብለዋል።
ከጎረቤት ኤርትራ ጋር የፈፀሙት የሰላም ስምምነት፣ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታታቸውና ለለውጥ ያላቸው ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ያሉት አምባሳደሯ፥ “ከእንዲህ አይነት መሪ ጋር እንዴት ወደ ፀብ ይገባል?” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
አፍሪካውያን ጋዜጠኞች፥ ከቅኝ ገዥነት አስተሳሰብ ነፃ ባልወጣው በምዕራቡ ዓለም ፕሮፓጋንዳ መነዳታቸውን አቁመው የአህጉሪቱን ጉዳይ በራሳቸው አቅም ነቅሰው በማውጣት የመፍትሄ አካል መሆን እንደሚገባቸውም ነው አምባሳደሯ ያሳሰቡት።
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ፥ ግብፅ የዓባይን ውሃ ለብቻዋ ለመጠቀም የምታሳየው ራስ ወዳድነት የተፋሰሱን አገራት መብት የሚጋፋ እኩይ ተግባር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የናይል ተፋሰስ አገራት የዓባይ ወንዝ በፈጣሪ የተበረከተላቸው ገፀ በረከት መሆኑን ተገንዝበው ለጋራ ተጠቃሚነት በመደጋገፍ ሊሰሩ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
በወንደሰን አረጋኸኝ
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.