Fana: At a Speed of Life!

በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በፈጸመው ወረራ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች 4 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።
ድጋፉን ያደረጉት በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ የፈረሳይ ለጋሲዮን ወጣቶች ኖርዌይ ሀገር ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንዲሁም ከመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር የተደረገ ነው።
በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 2 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዓለማየሁ ማሞ ወጣቶቹን ወክለው ዛሬ ድጋፉን ሲያስረክቡ እንዳሉት አሸባሪው ህወሓት ያደረሰውን ጉዳት ለመቋቋም የጋራ ትብብር ይጠይቃል።
በድጋፉ 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው 46 ቦንዳ አልባሳት እና ጫማዎች፣ 1 ሺህ 200 የመመገቢያ ሳህን፣ 73 ኩንታል የዳቦ ዱቄት፣ ፓስታና ማካሮኒ እንዲሁም 400 ብረት ድስቶች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
በተጨማሪም የሴቶችና የህፃናት ንጽህና መጠበቂያ እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁስ ወጣቶቹ በማሰባሰብ ለወገኖቻቸው መላካቸው አስረድተዋል።
በኖርዌይ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተወካይ ወይዘሮ ኢትዮጵያ ዓለማየሁ በበኩላቸው፣ “ድጋፉ በውጭ ያሉ ዜጎች ለተቸገሩ ወገኖች ያላቸውን ቀናኢነት የሚያረጋግጥ ነው።” ብለዋል።
እርሳቸውም ልጆቻውንና ቤታቸውን ትተው የመንግስትን የክተት ጥሪ ተቀብለው እናት አገራቸውን ለማገልገል ከውጭ ከመጡ ሁለት ወር እንዳለፋቸው አስረድተዋል።
ችግሩን በአካል ተገኝተው በማየታቸው በቀጣይ በይነ መረብን ተጠቅመው ተጨማሪ ሀብት በማሰባሰብ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚጥሩም አረጋግጠዋል።
የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር ተወካይ አቶ ጌታሁን በቀለ በበኩላቸው 400 ሺህ ብር ግምት ያለው አልሚ ምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ይዘው መምጣታቸውን ገልጸዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ከሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ተፈናቅለው የሚመጡ ዜጎች ቁጥር እጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።
ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኑሯቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ኢትዮጵያውያን፣ የተለያዩ ረጅ ድርጅቶችና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.