ፋርማ ኮሌጅ የ2013 ዓ.ም ተማሪዎቹን አስመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመማር ማስተማር ሒደቱ 18 አመታትን ያስቆጠረው ፋርማ ኮሌጅ የ2013 ዓ.ም ተማሪዎቹን በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ዛሬ አስመርቋል።
የኮሌጁ ፕሬዚዳንት አቶ ስዩም ከበደ ፥ በመጀመሪያ ዲግሪ በነርሲንግ፣ ፋርማሲ፣ ህብረተሰብ ጤና እና በሁለተኛ ዲግሪ በህብረተሰብ ጤና 272 ሴትና 280 ወንድ በአጠቃላይ 552 ተማሪዎች ማስመረቁን ገልጸዋል።
ኮሌጁ ከመማር ማስተማሩ በተጨማሪ ሀገራዊ ግዴታውን ለመወጣት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚውል 110 ሺህ ብር እንዲሁም ለተፈናቃዮች ድጋፍ የሚውል 50 ኩንታል ፍርኖ ዱቄት ፣ 4 ማዳበሪያ አልባሳት እና 1 ማዳበሪያ ጫማ በቀይ መስቀል በኩል መስጠቱን የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።
እኛ ዛሬ ተሰባስበን ለመመረቅና ማስመረቃችን ዋጋ እየከፈሉ ላሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይህ ድጋፍ ጥቂት ነውና ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያለው ኮሌጁ ፥ ከግንባር ተመልሰው በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ያሉ 155 ተጎጂዎችን መደገፍ እንደሚገባም ገልጿል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በምክትል ቢሮ ሀላፊ የቢሮው አማካሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ ኮሌጁ በክልሉ እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
ተመራቂ ተማሪዎቹ ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቃል የገቡ ሲሆን ፥ ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ ተደርጓል።
በመቅደስ አስፋው
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን