Fana: At a Speed of Life!

አዋጁ የባህር ዳር ከተማን ሰላምና ፀጥታ ከሰርጎ ገቦች መጠበቅ አስችሏል – ኮማንድ ፖስት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአግባቡ ተፈጻሚ በማድረግ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ከሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ መቻሉን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።

የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢና የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ለኢዜአ እንደገለፁት፥ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ህጎችን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ላይ ተገቢ እርምጃ እየተወሰደ ነው።

ዶክተር ድረስ እንዳሉት ሰሞኑን በቀን የተዘጋ ቤት ሰብሮ በመግባት ዝርፊያ የመፈጸም ወንጀል በከተማዋ ተስተውሏል።

ይህን ተከትሎ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ግማሾቹ ለዝርፊያና ህብረተሰቡን በማሸበር ሰላም ለማሳጣት ወደ ከተማዋ የገቡ ሰርጎ ገቦች መሆናቸውንም አስረድተዋል።

እንደ ዶክተር ድረስ ገለጻ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው፣ ለከተማዋ ሰላምና ደህንነት ስጋት ናቸው በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሥራ እየተከናወነ ነው።

ህገ ወጥ እንቅስቃሴን ለመግታትም በከተማዋ በተጠባባቂ ኃይልነት ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች አደረጃጀት ተፈጥሮላቸው ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን የተጠናከረ ጥበቃ እያካሄዱ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በርካታ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦችና ጥይቶች መያዝ መቻሉን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.