ለአሸባሪውና ወራሪው ኃይል የእግር እሳት የሆነው ሕዝባዊ ሠራዊት
አዲስ አበባ፣ ህዳር 04 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ በለሳ ወረዳ ሕዝባዊ ሠራዊት ከሌሎች የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ጋር በመቀናጀት በአሸባሪውና ወራሪው ኃይል ላይ ከባድ የማጥቃት እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ።
ለሀገሩ መሞት ክብርና ኩራቱ የሆነው ይህ ሕዝባዊ ሠራዊት “ለዘመቻ ወደ ኋላ የቀረህ ጥቁር ውሻ ውለድ” ብሎና ተማምሎ መነሳቱን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል።
በቆራጥነት እና አይበገሬነት ወኔ የተመመው ሕዝባዊ ሠራዊት ቀፎው እንደተነካ ንብ ከሁሉም አካባቢዎች ወደ ግንባር በመትመም የጠላትን አንገት እያስደፋ ነው።
የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ሕዝባዊ ሠራዊት ከዋግ ጀግኖች ጋር በመሆን ወራሪውን የትህነግ ቡድን መውጫ መግቢያ አሳጥቶታል።
የኪንፋዝ በገላ ወረዳ የሕዝባዊ ሠራዊቱ አባል አቶ እሸቴ ዳኛው፥ “የወረዳው ሕዝብ የክልሉን መንግሥት የክተት ጥሪ ተቀብሎ ዋግኽምራ ግንባር ዘምቷል፤ በግንባሩም ጠላትን እየደመሰሰ ለከፍተኛ ድል እየገሰገሰን ነው” ብለዋል።
ሕዝባዊ ሠራዊቱ ትጥቁን እና ስንቁን ይዞ መዝመቱን የገለጹት ዘማች እሸቴ ሕዝባዊ ሠራዊቱ ለዘመቻ ሲሄድ ቀያቸው እንዳይደፈር ተጠባባቂ ኃይል መዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡
አሸባሪውና ወራሪው ኃይል በአማራ ላይ ላይ እያደረሰ ያለው ጭፍጨፋ፣ዝርፊያ እና ውድመት እጅጉን ያንገበገባቸው ዘማቾቹ በሽብር ኃይሉ የተወረሩ አካባቢዎችም በቅርብ ቀን ነፃ ይወጣሉ ነው ያሉት።
ከልጃቸው ጋር ወደ ግንባር መዝመታቸውን የገለጹት ሌላኛው የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ዘማች አማረ ምስጋናው፥ ከዚህ በፊት ወራሪው ኃይል በጋይንት ግንባር ወረራ ለመፈጸም ሞክሮ ሳይሳካለት ተሰባብሮ በተመለሰበት ዘመቻ መሣተፋቸውን ተናግረዋል።
በዚያን ጊዜ ጠላት ደብረታቦር ከተማን ለመያዝ አሰፍስፎ ሲመጣ አከርካሪውን ሰብረን መልሰናል የሚሉት አቶ አማረ፥ ዛሬም በዋግ ግንባር ልጃቸውን ይዘው ታላቅ ጀብድ እየፈጸሙ መሆናቸውን ነው የሚናገሩት።
የኪንፋንዘ በገላ ወረዳ የሕዝባዊ ሠራዊቱ መሪ ሻምበል ተስፋየ አዛለው ከሌላው ሕዝባዊ ሠራዊት ጋር በመሆን በአንድነት፣ በጀግንነት እና ወኔ ጠላትን እየቀጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሻምበል ተስፋየ በግንባር የተገኘው ሕዝባዊ ሠራዊት ኢትዮጵያ ልጆቿ እያሉ የማትፈርስ ሀገር መሆኗን ያስመሰከረ ነው ብለዋል።
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
+2
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share