Fana: At a Speed of Life!

በሕዝቡና በጸጥታ አካላት ቅንጅት እየተገኘ ላለው ድል መንግሥት ምስጋና ያቀርባል -ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝቡና በጸጥታ አካላት የተቀናጀ ርብርብ እየተገኘ ላለው ድል መንግሥት ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።
ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዘሬ በሰጡት መግለጫ ፥ በመላው ኢትዮጵያ ዜጎች የሀገራቸውን ህልውና ለማስጠበቅና በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመቀልበስም ወደ ግንባር እየዘመቱ ነው ብለዋል።
አካባቢያቸውን በመጠበቅና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ያሳዩት ተሳትፎ የሚያኮራ እንደሆነ ገልጸዋል ።
ለህልውና የመዝመቱ እንቅስቃሴ በሁለት መንገድ ሲከናወን ቆይቷል።
በመላ ሀገሪቱ ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ያሉ ወጣቶች የህልውና ዘመቻውን ለማሳካት ወደ ግንባር በገፍ እየዘመቱ ነውም ነው ያሉት።
በተወረሩ አካባቢዎች ውስጥ ያሉ የአማራና የአፋር ክልል ነዋሪዎችም ዳግም ጭቆናን አንቀበልም በማለት አኩሪ ተጋድሎን እያደረጉ ወራሪውን ኃይል ከየተማውና በየቀዬው እያስወገዱ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢ የተቀጣጠለው ሀገር አቀፍ የአርበኝነት እንቅስቃሴ ከዳር ዳር እየተስፋፋ ይገኛል። የሕዝቡ ቆርጦ መነሣት በሀገሩ ህልውና እንደማይደራደር ለሁሉም ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል ሕዝቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እየጠበቀ ይገኛል። በዚህም ከጸጥታ አካላት ጋር በየሠፈሩ ወንጀል እንዳይፈጸም በመጠበቅ እያበረከተ ያለው አስተዋጽዖ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ነው ያሉት።
ሕዝቡ ለጸጥታ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። የህልውና ዘመቻው ከተጀመረ ጊዜ አንሥቶ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በደም ልገሳ፣ ስንቅ በማዘጋጀትና የሞራል ድጋፍ በመስጠት የዘመቻው ባለቤትነቱን በማሳየት ላይ ነውም ሲሉ ገልጸዋል።
ጠንካራ ደጀንነቱንም በተግባር እያረጋገጠ ነው። ይህ የተቀናጀ ርብርብ የአሸባሪ ቡድኑን የጥፋት ምኞትና ፍላጎት በየግንባሩ እያመከነው ይገኛል።
በተለያዩ ግንባሮችም የአሸባሪው ወራሪ ቡድን እየተመከተ፤ የተደቀነው የህልውና አደጋም እየተቀለበሰ ይገኛል።
በኦሮሚያ ክልል በሳምንቱ በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ የሚገኘው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በተለይም በምዕራብና ሰሜን ሸዋ እንዲሁም በምዕራብ ወለጋና ሆሮጉድሩ የህወሃት አሸባሪ ቡድን ተላላኪው ሸኔ ዳግም ሊያንሰራራ በማይችልበት ደረጃ እርምጃ እየተወሰደበት ይገኛል።
በሕዝቡና በጸጥታ አካላት የተቀናጀ ርብርብ እየተገኘ ላለው ድል መንግሥት ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባልም ነው ያሉት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.