Fana: At a Speed of Life!

ማዕቀቡ አጥቂውን ትቶ ተጠቂው ላይ በትር ማሳረፍ ነው – ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ኢትዮጵያ አወገዘች፡፡
በኤርትራ መንግሥት እና በአንዳንድ አመራሮች ላይ አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ አግባብ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ፡፡
ማእቀቡ አጥቂውን ትቶ ተጠቂው ላይ በትር ማሳረፍ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ማዕቀቡን ተገቢነት የሌለው እንደሆነ ያምናል ሲል የውጭ ጉይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከሕወሓት አሸባሪ ቡድን የተሰነዘረበትን ጥቃት ለመመከትና የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር በተገደደው የኤርትራ መንግሥት ላይ ማዕቀብ መጣል ለቀጣናው ሰላም እንደማይበጅ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚገነዘብም ነው በመግለጫው የተመላከተው፡፡
የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ÷ የአሜሪካ መንግስት የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ የኢትዮጵያ መንግሥት ጠይቋል፡፡
1. ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት ሀገር በሆነችው ኤርትራ ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል።
2. የኤርትራ መንግስት በግዛቱ አንድነት እና ደህንነት ላይ ለተቋጣው ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሉዓላዊ መብት አለው።
3. የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ግዛቱን አልፎ መገኘቱን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቅሬታ አለማቅረቡንም መግለጫው አስታውሷል።
እንዲህ ዓይነት ቅሬታ የማቅረብ መብት ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ እንጂ ሌላ አካል አይደለም።
4. የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀውን የተናጥል የሰብአዊ መብት ተኩስ አቁም ተከትሎ ወታደራዊ ሀይሉን ከኢትዮጵያ ማስወጣቱም ይታወቃል።
5. የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን የኤርትራ መንግስት እንቅፋት ነው ብሎ አያምንም።
በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የሰላም ስጋት የህወሓት ጠብ አጫሪነት እና ወረራ ነው።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሓትን የማተራመስ ሚና አጥብቆ ለማውገዝ አለመፈለጉም የሽብር ቡድኑን እንዳበረታታው ኢትዮጵያ ታምናለች ብሏል መግለጫው፡፡
የማዕቀቡ አላማ የተፈጠረው ቀውስ እንዲቆም ለማስገደድ ከሆነ፣ የአሜሪካ መንግስት እና የዓለም ማህበረሰብ ትክክለኛ ማዕቀብ እና ተጨማሪ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ኢላማው በህወሓት ላይ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ መንግስት በፅኑ ያምናል።
ስለዚህ የአሜሪካ መንግስት በኤርትራ ላይ የወሰደውን ማዕቀብ እንዲሰርዝ እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፈተናዎች ዋነኛ መንስኤ የሆነውን አሸባሪውን ህወሓት በመቃወም እርምጃ እንዲወስድ በአፅንኦት እንጠይቃለን ብሏል መግለጫው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.