Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን ባርነትን የሚሸከም ጫንቃ የለንም – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ህዳ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እኛ ኢትዮጵያውያ ባርነት ለመሸከም የተዘጋጀ ጫንቃ የለንም ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
የጀመርነው ትግል የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አስጠብቆ ለማስቀጠል በቆሙ እና እስከወዲያኛው ስንዴ እየተሰፈረላት፣ እጇ እየተጠመዘዘ፣ እያነሰችና እየተዋረደች እንድትኖር ለማድረግ ጋብቻ በፈፀሙ ፀረ ኢትዮጵያ ሀይሎች መካከል የሚደረግ ትግል ነዉ ብለዋል፡፡
አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ካልሆነ ነገሩ÷ ኢትዮጵያውያን ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከሃገር ውስጥ እስከ ውጪ በአደባባይ በነቂስ በመውጣት አምርሮ ኢትዮጵያን ለመጠምዘዝ የሚደረጉ ሙከራዎችን አውግዘዋል ብለዋል፡፡
በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ልጆች÷ መተኪያ ከማይገኝላት ከዉዷ አገራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች በአካል ርቃችሁ ብትኖሩም “ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊም መልኩን ” እንዲሉ በኢትዮጵያ ላይ የዉስጥ ባንዳዎች እና የዉጪ እጅ ጠምዛዦች በአንድነት የተከፈተብንን የተቀነባበረ ዘመቻ፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ክብር የሚነካ ጣልቃ ገብነት ተቃዉማችሁ በአደባባይ በአንድነት ድምፃችሁን በማሰማታችሁ ኮርተንባችኋል÷ ትዉልድም የአገር ፍቅርን ይማርበታል ብለዋል ወይዘሮ አዳነች።
ዉድ የአገሬ ልጆች የጀመርነውን የተቀናጀ ትግል አጠናክረን እንቀጥል፤ ጦርነቱ ዘርፈብዙ ነውና ብዙ ዋጋና መስዕዋቶችን መክፈልን ይጠይቀናል ብለዋል፡፡
ከአንዳንዶቻችን የንብረት፣ የአካል፣ የህይወት ዋጋ ክፍያን የሚጠይቅ ሲሆን÷ ሌሎቻችን ደግሞ በሰዉ አገር ባይተዋርነት፣ እንግልት፣ የሃገራችሁን እውነት ጫና፣ ዉክቢያ እንዲሁም ስድብና ማመናጨቅን ተቋቁሞ ማለፍን ይጠይቃል ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በያለንበት በአንድነት ስለሃቅ የምናደርገው ትግል ድምር ዉጤት አሸናፊዎች እንደሚያደርገን እውነት ነው ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.