Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያንና ሚዲያዎቻቸው በኢትዮጵያ ላይ የሚያስተጋቡት መረጃ የተዛባ ነው – ሚሲዮናውያን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን እና ሚዲያዎቻቸው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የያዙት አቋም እና የሚያስተላልፉት ዘገባ ከእዉነት የራቀ ነዉ ሲሉ ከአሜሪካ የመጡ ሚሲዮናውያን ገለጹ፡፡
የአሜሪካ ዜጐች አርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናትና የሀገር የሽማግሌዎች አቀባበል አድርገዉላቸዋል።
70 አባላትን የያዘው “ሚሽን ጂሰስ ፎር ሚኒስትሪ” የተሰኘው የአሜሪካውያን ሚሽነሪዎች ቡድን በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የሚሽን ጂሰስ ሚኒስትሪ መስራችና ባለቤት አንድሬ ሻፕቫሌ ምዕራባውያን፣ አሜሪካ እና ሚዲያዎቻቸው ከእዉነት የራቁ መረጃዎችን እያሰራጩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ይህ እዉነትን ካለመፈለግ የመነጨ ስለሆነ በዉጭ ሀገራት ለሚገኙ ሁሉ፣ ኢትዮጵያ አሁን እጅግ ሠላማዊ መሆንዋን ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ማወቅ አለበት ብለዋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ የመጣችው የማህበሩ አባል ባየችዉ ነገር እጅግ ደስተኛ መሆኗንና አዲስ አበባን ጨምሮ አርባምንጭ ለደህንነታቸው የሚያሰጋ አንድም ነገር እንዳላጋጠማቸው ተናግራለች፡፡
ወደ ኢትዮጵያ የመጡ እንግዶች ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ትክክለኛ እዉነት ለተቀረው ዓለም ለማስረዳት ፋይዳዉ የጎላ ነው ሲሉ የማህበሩ አባላት መናገራቸውን ዴሬቴድ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.