Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት ለ5ኛ ጊዜ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበበ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ዞን በህልውና ዘመቻው በግንባር እየታገለ ላለው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአምስተኛ ጊዜ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
ዛሬ ለአምስኛ ዙር በተደረገዉ ድጋፍ÷ ከ 14 ሚሊየን ብር በላይ ብር በመከላከያ አካውንት ገቢ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም 370 ሰንጋዎች፣ 332 ፍየሎችና በጎች እንዲሁም 10 ነጥብ 5 ኩንታል ስኳር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ 199 ዩኒት ደም ልገሳም ተደርጓል፡፡
የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ የዞኑ ነዋሪዎች ለመከላካያ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ በቀጣይም ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከወላይታ ዞን የተወጣጡ ሀገር ለማዳን ለጥሪው ምላሽ የሰጡ አመራሮች፣ ተመላሽ ሰራዊት
አባላትና ተጠባባቂ ኃይል ወደ ግንባር ተሸኝተዋል፡፡
በማቱሣላ ማቴዎስ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.