Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው በሚችለው ሁሉ ኢትዮጵያን የሚደግፍበት ጊዜው አሁን ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው በገንዘቡና በእውቀቱ ኢትዮጵያን የሚደግፍበት ጊዜው አሁን ነው ሲል አርቲስት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ ገለጸ።
ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት በኢትዮጵያ ላይ የተጋረጠው የሕልዉና አደጋ ለመመከት በሚደረገዉ ጥረት የመፍትሔ አካል ለመሆንም ነው ብሏል፡፡
አርቲስት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ይህን ያለው ወደ ኢትዮጵያ የመጣበትን ዓላማና ከኢትዮጵያውያን የሚጠበቁ የጋራ የቤት ስራዎችን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡
አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ የጋረጠውን አደጋ ለመመከት ኢትዮጵያውያን በጋራ መቆም እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ለሀገራችን ኢትዮጵያ ያለናት እኛ ኢትዮጵያውያን ነን ያለዉ ታማኝ÷ ሁሉም ዜጋ ለአገሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ አማካኝነት ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚደረግም ተናግሯል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.