Fana: At a Speed of Life!

እርዳታና ብድር መከልከል ምዕራባውያን እጅ ለመጠምዘዝ የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካውያን የውጭ ተጽዕኖዎችን በጋራ በመመከት በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች ጠንካራ አህጉር ለመገንባት በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን ገለጹ፡፡
ምዕራባውያን አፍሪካ ላይ ጫና በመፍጠር ጥቅማቸውን ለማስከበር እየሰሩ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
እርዳታና ብድር መከልከልም÷ ምዕራባውያኑ የአፍሪካ አገራትን እጅ ለመጠምዘዝ የሚጠቀሙበት መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡
ምዕራባውያን ዋነኛ የንግድ መተላላፊያ መስመር በሆነው የቀይ ባህር ኮሪደር ጠንካራ አገርም ሆነ መንግስት እንዲፈጠር እንደማይፈልጉ ጠቁመው÷ የቀጣናው ሀገራትም ህብረት እንዲፈጥሩ አይፈልጉም ሲሉ ፕሮፌሰሩ አብራርተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ኤሲያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህር ዶክተር መሀመድ ሐሰን በበኩላቸው÷ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ መሪነት በምስራቅ አፍሪካ እየመጣ ያለውን ትብብር አይፈልጉትም ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው የተቀናጀ የውጭ ተጽዕኖ ደግሞ ለዚህ ዋነኛ ማሳያ መሆኑን የጠቆሙት ምሁሩ÷ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የምታራምደው የወንድማማችነት አካሄድ በአንዳንድ የምዕራቡ ዓለም አገራት ጥርስ እንድትገባ አድርጓታልም ብለዋል፡፡
ታላቁ የህዳሴ ግድብ አፍሪካ የማንንም እርዳታ ሳትሻ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ትምህርት የሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በማጠናከርና ችግሮቻቸውን በመፍታት የምዕራባውያንን ጫና መመከት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡
ምዕራባውያን አፍሪካን ለጥቅማቸው እንደሚፈልጓት የገለጹት ምሁራኑ÷ ከዚህ አኳያ አፍሪካውያን በየትኛውም ሀገር ላይ የሚደረግ የውጭ ጫናን በጋራ በመመከት ጠንካራ አህጉር የመፍጠር ኃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ አህጉር እንድትሆን የሚያስችሉ ዘዴዎቸን ቀይሶ መንቀሳቀስ እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡
የአፍሪካውያን ምሁራን የአፍሪካን ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና መጫዎት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.