Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ከተማ የሁላችን የበጎ አድራጎት ማህበር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ100ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ማህበሩ ለመከላከያ ካደረገው የብር ድጋፋ ባሻገር÷ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ሳሙና፣ ዱቄት፣ የምግብ እህል እና አልባሳትን ጨምሮ ከ40 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የማህበሩ ሊቀመበር አቶ ሳሙኤል በላይ÷ የሁላችን የበጎ አድራጎት ከዚህ በፊትም በበጎ አድራጎት ስራዎች እየተሳተፈ መሆኑን ገልፀው÷ በአሁኑ ወቅትም በግንባር መሥዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል እኛ ከጎናቸው መሆን ይኖርብናልም ብለዋል ።
የምስራቅ ዕዝ 25ኛ ክፍለ ጦር አባል ሻለቃ እሸቴ ታዘዘው በበኩላቸው÷ ማህበሩ በደጀን ላሉ የመከላከያ ሰራዊት ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ እንደሀገር የተጋረጠብንን የህልውና ዘመቻ በተባበረ ክንድ እንመክተዋለን ብለዋል ሲል የሶማሌ ክልል ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.