Fana: At a Speed of Life!

አገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን – የአራዳ ክፍለ ከተማ ሴቶች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአገር መከላከያ ሠራዊት ስንቅ ከማዘጋጀት ባሻገር የሚጠበቅባቸውን ሌሎች አገራዊ ግዴታዎችን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የአራዳ ክፍለ ከተማ ሴቶች ገለጹ፡፡
የክፍለ ከተማው አስተዳደርና የእናት አገር ጥሪ ኮሚቴዎች ባስተባበሩት የደረቅ ስንቅ ዝግጅት የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ለሠራዊቱ የሚሆን የደረቅ ምግቦች ስንቅ የማዘጋጀት ሥራ በይፋ ተጀምሯል፡፡
በስንቅ ዝግጅቱ የተሳተፉ ሴቶች ከስንቅ ዝግጅት ባለፈ የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ግዴታ ለመወጣት ያላቸውን ተነሳሽነት ገልጸዋል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት ሴቶች ለአገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ደጀንነት ለመግለጽ በስንቅ ዝግጅቱ በመሳተፋቸው ደስተኞች መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡
የመዲናዋ ነዋሪዎች የአካባቢያችንን ሠላም በመጠበቅ አገራዊ ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉም አክለዋል፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አባወይ ዮሐንስ አገር በአሸባሪው ኃይል የገጠማትን ተግዳሮት ለማለፍ ሁሉም በአቅሙ አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
ስንቅ የማዘጋጀቱ ተግባር ክፍለ ከተማው ከእናት አገር ጥሪ ኮሚቴዎች ጋር በመቀናጀት ማስጀመሩን ገልጸዋል።
ከስንቅ ዝግጅቱ በተጨማሪ ባለፉት አምስት ቀናት 39 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ሀብት ለመከላከያ ሠራዊት ማሰባሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
የመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ÷ ሕዝቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.