Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ እና አልሚ ምግብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሚድ ዋይፈሪዎች ማህበር በአማራ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ጤና ተቋማትና ለተፈናቀሉ ወገኖች 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የሕክምና ቁሳቁስና አልሚ ምግብ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተደረገ መሆኑም በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተመላክቷል።
አሸባሪው ህወሓት በክልሉ ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።
የኢትዮጵያ ሚድ ዋይፈሪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ዘነበ አካሉ ድጋፉን ሲያስረክቡ እንዳሉት፤ አሸባሪው ቡድን በፈጸመው ወረራ ህጻናት፣ እናቶችና አዛውንቶች ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል።
ዛሬ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች፣ መድሃኒቶች እና የህጻናት አልሚ ምግብ ድጋፍ አስረክበዋል።
ድጋፉ አሸባሪው ህወሓት በህብረተሰቡ ላይ ካደረሰው መጠነ ሰፊ ጉዳት አንጻር ውሱን መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይ ማህበሩ መሰል ድጋፎችን እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
በጤና ሚኒስቴር የእናቶች ጤና ቡድን አስተባባሪ ወይዘሮ ዘምዘም መሀመድ፤ ሚኒስቴሩ ችግሩ ከተፈጠረ ጀምሮ ለተፈናቃዮችና ለወደሙ የጤና ተቋማት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
“ከሚፈናቀሉ እናቶች መካከል አራት በመቶ የሚሆኑት ነፍሰ ጡሮች ናቸው” ያሉት ወይዘሮ ዘምዘም፤ በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለእናቶች፣ ለህጻናትና ለአዛውንቶች ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ አመልክተዋል።
አስተባባሪዋ እንዳመለከቱት፤ ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ረጅ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በመተባበር የሕክምና ቁሳቁስ፣ መድሃኒት፣ አልሚ ምግቦችና ሌሎች ግብዓቶችን ለማሟላት ጥረት እያደረገ ነው።
በአማራ ክልል ተፈናቃይ ወገኖች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።
“አሸባሪው ህወሓት በወረራቸው አካባቢዎች 29 ሆስፒታሎች፣ 258 ጤና ጣቢያዎች እና 941 የጤና ኬላዎች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል” ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አማረ ሰጤ ናቸው።
አሸባሪው ህወሓት በክልሉ የፈጸመውን ወረራ ለመቀልበስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
“በቀጣይ ተፈናቃዮችን ከመደገፍ ባለፈ ህብረተሰቡንና አጋር አካላትን በማስተባበር የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ” ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሚድ ዋይፈሪዎች ማህበር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ላደረገው ድጋፍ በተፈናቃይ ወገኖች ስም ምስጋና ያቀረቡት አቶ አማረ፣ መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.