የሀገር ውስጥ ዜና

የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

November 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ለ5ኛ ዙር ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በገንዘብና በአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

አሸባሪው ህውሓት በኢትዮጵያን ህዝብ ላይ የደቀነውን የህልውና አደጋ በመረዳት ግንባር ላይ ለሚገኘዉ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የሚሆኑ ድጋፍ ሲያሰባስብ መቆየቱን የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አክሊሉ ለማ ገልጸዋል፡፡

የወላይታ ህዝብ ያለውን ሁሉ ሳይደበቅና ሳይሸሽ የሀገራችን ህልውና ለማስጠበቅ ያደረገውን ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡

የወላይታ ህዝብ እስካሁን ድረስ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ያደረገዉን ድጋፍ በዞኑ አስተዳደር ስም አቶ አክሊሉ አመሰግነው ÷ መከላከያ ሰራዊቱ የህግ ማስከበር ተልዕኮውን እስከሚያጠናቅቅ ድረስ ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች ከጎኑ እንደሚቆሙ ጠይቀዋል።

አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ በዱር በገደሉ መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአምስተኛው ዙር ከ40 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብና በአይነት ድጋፍ መደረጉን የወላይታ ዞን ሀብት አሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እታገኝ ኃለማርያም አስታውቀዋል።

የሀብት አሰባሰቡ በጥሬ ገንዘብ ከአስራ አምስት ሚሊየን ብር በላይ ፤ ከሃያ አምስት ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የዞኑ ሀብት አሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እታገኝ መግለጻቸውን ከደሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን