የስልጤ ዞን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስልጤ ዞን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በ4ኛው ዙር የሀብት አሰባሰብ መርሃግብር ከ18ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሀብት መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡
የዞኑ ሴቶችና ወጣቶች የ4ኛው ዙር የሀብት አሰባሰብ መርሃ ግብር አካል የሆነ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሰንባች ስንቅ፣ ሙክትና ሰንጋ ለዞኑ ሀብት አሰባሳቢ ግብረ ኃይል አስረክበዋል።
በርክክብ ስነስርዓቱ ላይም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ÷ይህን የሰው ዘር ጠላት የሆነውን የህወሓት ኃይል ኢትዮጵያ ሀገራችን ባቀረበችው ጥሪ መሠረት መላው የስልጤ ህዝብ የሞራል ስንቅ በመሆን፣ ልጆቹን ወደ ግንባር በማዝመትና ሀብት አሰባስቦ በመላክ የጀግንነትና የደጀንነት አለኝታነቱን በብቃት ማረጋገጥ የቻለ ኩሩ ህዝብ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው አብራርተዋል።
እንደዞንም ባለፉት ጊዜያት 4 ዙር የሀብት አሰባሰብ መርሃ ግብር ማህበረሰቡ ሀገርን በማስቀደም ሳይሰስት ባደረገው መጠነ ሰፊ ርብርብ እስካሁን ባለው ከ58ነጥብ 1 ሚለየን ብር በላይ ሀብት መሰብሰቡን ዋና አስተዳዳሪው አብራርተዋል።
የዞኑ ሴቶች ከ1ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ ሰንባች ምግቦችን በማዘጋጀትና የዞኑ ወጣቶችም ከ1ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የበግና የፍየል ሙክት እንዲሁም የበሬ ሰንጋ በድምሩ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሀብት በማሰባሰብ ነው ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ በማድረግ አለኝታነታቸውን ያረጋገጡት።
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይም ሴቶችና ወጣቶቹ ባስተላለፉት መልእክት የተጀመረው ዘመቻም በድል እስኪጠናቀቅ ድጋፋቸውን በቀጣይ በተሻለ ሁኔታ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ማረጋገጣቸውን ከደሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን