Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ከ380 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ህዝብ እና መንግስት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ380 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የክልሉ ህዝብ እና መንግስት የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለሚፋለመው መከላከያ ሰራዊት ያደረጉት የድጋፍ መርሐ ግብር ዛሬ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ክልሉ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ባደረገው ድጋፍ ርክክብ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጂ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ይካሄዳል።

በሌላ በኩል ከክልሉ ወደ መከላከያ ሰራዊቱ ለሚቀላቀሉ አመራሮች እና ህዝባዊ ሰራዊት የሽኝት መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.