16 የዞን አመራሮች የህልውና ዘመቻ ጥሪውን በመቀበል በዘመቻው ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014(ኤፍ ቢሲ) 16 የዞን አመራሮች የህልውና ዘመቻ ጥሪውን በመቀበል በዘመቻው ተቀላቅለዋል፡፡
የህልውና ዘመቻውን ከተቀላቀሉ ከዞኑ አመራሮች መካከል አቶ ወርቁ ቡዜ እና አቶ ሠራዊት ገዘኸኝ ÷ አመራር እንደመሆናችን መምራት የምንችለው ሰርተን ማግኘት የሚቻለው ፣ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚቻለው ሀገር ሲኖር ነው ።
በመሆኑም በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የኢትዮጵያን ክብርና ሰላም ለማስጠበቅ አመራር እንደመሆናችን ለሌሎችም ምሳሌ እንዲሆን ዘመቻውን በመቀላቀላችን ታላቅ ክብርና ታሪካዊ ኩራት ይሰማናል ብለዋል ።
የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ቲቆ ትላንቴ ÷ የጋሞ ዞን ብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይልና በክብር የተሰናበቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲሁም የዞኑ 16 አመራሮችን ጨምሮ 41 ዘማቾች በፈቃዳቸው ዘመቻውን እንደተቀላቀሉ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የተቃጣው የጠላት ሴራ በሙሉ እስኪጠፋና የአሸባሪዎች ተልዕኮ እስኪፈርስ ወታደራዊ እና ሁለንተናዊ ትግሉን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ።
ዘመቻውን የተቀላቀሉት በክብር ተሠናባችና ብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይሎች በበኩላቸው ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በመቀላቀል የሀገራችንን ሠላም እናረጋግጣለን ብለዋል።
በጋሞ ዞን ለሀገር ህልውና የሚደረግ ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች ተጠናክሮ መቀጠሉን ከጋሞ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!