Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደርና ህዝብ ለጀግናዉ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና በደብረብርሀን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ ።

በግንባር ተገኝተዉ ድጋፉን ያበረከቱት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ጋዲሳ እንደተናገሩት ÷ የመከላከያ ሰራዊታችን ጁንታዉን ለመቅበር ፊትለፊት እንደተጋፈጠዉ ሁሉ እኛ ደግሞ ከኋላ ደጀን የመሆን ሀገራዊ ግዴታ ስላለብን ግንባር ተገኝተናል ብለዋል፡፡

አጠቃላይ 120 የሚሆኑ ሰንጋዎች እና ከ100 ኩንታል በላይ ዱቄት ነዉ ድጋፍ የተደረገዉ፡፡

መከላከያ ሚኒስትርን በመወከል ድጋፉን የተረከቡት ብርጋዴር ጄነራል ቡልቲ ታደሰ እንደተናገሩት ÷ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመቅበር እያደረጉ ያሉት ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡

አሁንም ግብአተ መሬቱ እሰከሚጠናቀቅ ድረስ የሚወሰደዉ እርምጃ እንደማይቆም ገልፀዉ ÷ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደርና ህዝብ ላደረገላቸዉ ድጋፍ አመሰግነዋል፡፡

በብስራት መንግስቱ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.