የሀገር ውስጥ ዜና

በቡታጅራ ከተማ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

By Meseret Awoke

November 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡታጅራ ከተማ አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝና መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

ክልል አቀፍ በሆነው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ “አሸባሪው የህውሓት ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ነው! የሀገራችንን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ እስከ ግንባር እንዘምታለን!” በማለት ድምጹን አሰምቷል።

ሰልፈኞቹ ካሰሟቸው ሌሎች መፈክሮች መካከል ፥ “ሁላችንም በየተሰማራንበት መስክ የህልውና ዘመቻው አካል ነን! የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የሚነዙብንን ሚዲያዎች እናወግዛለን! ሀገራችን ኢትዮጵያን ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች እንታደጋለን!” የሚሉ ይገኙበታል።

በሰልፉ ሥነ ስርዓት ላይ የክልል፣ የዞን፣ የከተማ አስተዳደርና የወረዳ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!