Fana: At a Speed of Life!

አራዳ ክ/ከተማ ለመከላከያ ሠራዊት ከ41 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አሰባሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ለአገር መከላከያ ሠራዊት በ8 ቀናት ብቻ ከ41 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማሰባሰቡን ገለጸ።
 
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አባወይ ዮሃንስ “ህብረተሰቡ መከላከያ ሰራዊቱን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በመደገፍ ደጀንነቱን በተግባር ማሳየቱን ቀጥሏል” ብለዋል።
 
ይህም ህብረተሰቡ ሰራዊቱን ለመደገፍና ለሌሎችም ተግባራት ያለውን ተነሳሽነትና አንድነት የሚያመላክት ሲሆን የዜግነት ድርሻውን ለመወጣት ያለውን ቁርጠኝነትም የሚያሳይ ነው ብለዋል።
 
“በክፍለ ከተማችን በ8 ቀን ውስጥ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ማሰባሰብ ችለናል” ነው ያሉት።
 
ከዚህ ጎን ለጎን የክፍለ ከተማው ማህበረሰብ በሁሉም ወረዳዎች በበጎ ፈቃደኝነት የስንቅ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
 
ከድጋፉ በተጨማሪ በርካታ ወጣቶች የአገር መከላከያ ሰራዊትን እየተቀላቀሉ መሆኑን ጠቅሰው፤ “ሁሉም ኢትዮጵያውያን በመዝመት፣ ሰራዊቱን በመደገፍ፣ አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ በዘመቻው ሊሳተፉ ይገባል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.