Fana: At a Speed of Life!

መስዋዕትነት በመክፈል ህልውናችን የምናረጋግጥበት ጊዜው አሁን ነው-አቶ ፍስሃ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ ውጤታችን የሚመዘነው የሽብር ቡድኑን ህወሓት በመቅበር ህልውናችንን ማረጋገጥ ስንችል ነው አሉ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ደሳለኝ።
 
በጋይንት-ጋሸና ግንባር የገባውን የትህነግ ወራሪ ሃይል ለመደምሰስ እና እስከወዲያኛው ለመቅበር የሚያስችል ግምገማ በዛሬው እለት ተካሂዷል።
 
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ሲሳይ÷ የተደራጀው ኀይል መስዋዕትነት እየከፈለ ታሪክ ለመስራት የሚጠበቅበትን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
 
የአካባቢው ህዝብም ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን ነው የተናገሩት።
 
የአብክመ የገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በበኩላቸው÷ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።
 
ሁሉም የድርሻውን በመፈጸም ወራሪውን ኅይል የሚወገድበትን ጊዜ ማሳጠር እንደሚገባም አንስተዋል።
 
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ደሳለኝ÷ የስራ ውጤታችን የሚመዘነው በምናስመዘግበው ድል ላይ በመመስረት ነው ብለዋል።
 
የተነሳንበት ዓላማ የትግራይን ወራሪ ኀይል በመቅበር ህልውናችንን ማረጋገጥ ነው ያሉት ሃላፊው ÷ የስራ ውጤታማነታችን የሚለካው ከዚህ ዓላማና ግባችን ስኬት አኳያ ተመዝኖ መሆን አለበት ብለዋል።
 
ህይወት በመስጠት ነፃነታችን የምናስከከብርበትና ህልውናችንን ማረጋገጥ የግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ብቸኛ አማራጫችንም ማሸነፍ ነው ሲሉ መግለጻቸውን ከፓርቲው ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.