Fana: At a Speed of Life!

የጌዲኦ ዞን ነዋሪዎች ለሰራዊቱ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የጌዲኦ ዞን ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ።
 
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ደርቤ ጅኖ÷ድጋፉን ለመከላከያ ህብረት ሎጂስቲክስ መምሪያ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ሹማ ኦብሳ አስረክበዋል።
 
በዞኑ ከተደረገው ድጋፍ 7 ሚሊየኑ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን÷ ቀሪው ደግሞ በአይነት መሆኑን ልዩ አማካሪው ገልጸዋል።
 
በአይነት ከተደረገው ድጋፍ 6 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ግምት የሚያወጡ 172 ሰንጋዎች፣ 114 በጎች እንዲሁም 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ግምት የሚያወጣ ስንቅ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ከአይነትና ገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ የዞኑ አመራሮች የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን መሰለፋቸውንም ተናግረዋል።
 
ህብረተሰቡ አሸባሪውን ህወሃት ለመደምሰስ እየተዋደቀ ላለው ሰራዊት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው የጠባለው፡፡
 
ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት የመከላከያ ህብረት ሎጅስቲክስ መምሪያ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ሹማ ኦብሳ÷ የጌዲኦ ዞን ነዋሪዎች የህልውና ዘመቻው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተደጋጋሚ መሰል ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል መባሉን ኤዜአ ዘግቧል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.