Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓትን ለሚደግፉ ኃይሎች የማረጋግጠው ኢትዮጵያ እንደምታሸንፍ ነው-ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ ህወሓት ባለፉት 27 ዓመታት የፌዴራል ስርአቱን በተሳሳተ መንገድ በመጠቀም የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት በተጠና መልኩ ሲጥስ እንደነበር የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ገለጹ፡፡
 
ሚኒስትር ዲኤታው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ከህንዱ ዲዲ ሚድያ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
 
በቆይታቸውም አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት የሽብር ቡድኑ ህወሓት በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለመቀልበስ በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተጀመረ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
 
የህግ ማስከበር ዘመቻው ከተጠናቀቀ በኋላም መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም በማድረግ ከትግራይ ክልል መውጣቱን አንስተዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ የሽብር ቡድኑ አጋጣሚውን በመቀጠቀም እና ዜጎችን በተሳሳተ መንገድ በአስገዳጅ ሁኔታ በመቀስቀስ በአማራ እና አፋር ክልሎች ወረራ መፈጸሙን ነው የገለጹት፡፡
 
የሽብር ቡድኑ ህወሓት ባለፉት 27 ዓመታት የፌዴራል ስርዓቱን በተሳሳተ መንገድ በመተግበር የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በተጠና መልኩ በመከፋፈል እና ቅራኔ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ መብታቸውን መልኩ ሲጥስ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
 
ለአብነትም ሲዳማ እና ሌሎች ህዝቦች ላለፉት አመታት ሲያቀርቡት የነበረውን የክልልነት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጥያቄውን በሃይል ሲያፍን መቆየቱን አንስተዋል፡፡
 
በአንፃሩ አሁን ላይ የለውጡ መንግስት የፌዴራል ስርዓቱን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመተርጎም ህዝቦች ለሚያነሱት ጥያቄ ተገቢ ምለሽ መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
 
ሚኒስትር ዲኤታው አሸባሪው ህወሓትን ለመደግፍ ለሚሞክሩ ኃይሎች የማረጋግጠው ኢትዮጵያ እንደምታሸንፍ ነው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
 
አሸባሪው ቡድን ከውጭ ሃይሎች የሳተላይት እና ሌሎችም ድጋፎች እንደሚያገኝም ተናግረዋል፡፡
 
ይህም በማስረጃ መረጋገጡን ጠቅሰው፥ የኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት ለአጠቃላይ የቀጠናው መረጋጋት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.