አሸባሪውን ህወሓት ተጠያቂ ለማድረግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ሊያሳድር ይገባል -አቶ ሌንጮ ለታ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሞኑን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ተከትሎ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአሸባሪው ሕወሓት ጦር በአማራ ክልል ንፋስ መውጫ አካባቢ በፈፀማቸው ወንጀሎች ተጠያቂ እንዲሆን ጫና ሊያደርግ እንደሚገባ አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ሌንጮ ለታ ገለጹ፡፡
አቶ ሌንጮ ለታ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በአሸባሪው ሕወሓት ቀስቃሽነት የተጀመረው ጦርነትን ተከትሎ የተፈፀሙ ግድያ፣ ዘረፋና በቡድን ሴቶችን የመድፈር ወንጀሎችን በማጣራት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ለኢፕድ እንደገለጹት÷ አሸባሪው ቡድን በፈፀማቸው ወንጀሎች ተጠያቂ እንዲሆን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጫና ማድረግ ይገባዋል፡፡
ጫና ብቻ ሳይሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግም አለበት ነው ያሉት፡፡
በጦርነት ወቅት በቡድን ሴቶችን መድፈር በዓለም አቀፍም ሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው፤ በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ ዘንድም አስነዋሪ ድርጊት ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን ይህንን አሳዛኝ ድርጊት መፈፀሙ ለሕዝብ ያለውን የጭካኔ ጥግ ማሳያ በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ድርጊቱን በጋራ በማውገዝ መንግሥት አሸባሪውን ቡድን በፈፀመው ወንጀል ልክ ተጠያቂ እንዲያደርግ ግፊት ሊያደርጉ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያም መንግሥት በአግባቡ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ነው የገለጹት፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን