Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከዛሬ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ክትባት በዘመቻ መልክ ይሰጣል

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለተከታታይ 10 ቀናት በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

በዚህም ክትባቱ እድሜያቸው 12 ዓመትና ከዚያን በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጥ የአበባ ከተማ ጤና ቢሮ የገለጸ ሲሆን ÷በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጤና ጣቢያ በመሄድ ክትባቱን መውሰድ እንደሚችሉ የቢሮው ሃላፊው ዶክተር ዮሃነስ ጫላ አስታውቀዋል።

ከጤና ጣቢያዎች በተጨማሪም የክትባቱን ተደራሽነት ለማስፋት በትላልቅ የገበያ ቦታዎች ፣ ሞሎች ፣ በባንኮች ፤ በትራንሰፖርት መናህሪያዎች ፤ በኢንዱስትሪ ፓርክ እና በሌሎች የተመረጡ ቦታዎች ይሰጣል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ እስከአሁን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች የኮቪድ 19 ክትባት የተሰጠ ሲሆን÷ ለ10 ቀናት በሚካሄደው የክትባት ዘመቻ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ የክትባት ቡድኖች መደራጀታቸውን ዶክተር ዮሃንስ ጫላ ገልጸዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.