የጠላትን ግፍ ለማስቆም መከፈል የሚገባውን መስዋእትነት እንከፍላለን- የአማራ ሳይንት ሚሊሻዎች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠላትን ግፍ ለማስቆም መከፈል የሚገባውን መስዋእትነት እንከፍላለን ሲሉ የአማራ ሳይንት ሚሊሻዎች ተናገሩ፡፡
ሚሊሻዎቹ ጠላትን ለመደምሰስ የተሰጣቸውን ግዳጅ በጥሩ ሁኔታ እየተወጡ መሆኑን እና አሁንም የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡
ለጠላት እጅ የሚሰጥ የለም፣ እናሸንፋለን ያሉት ሚሊሻዎቹ ለየትኛውም ትግልም ቆራጥ መሆናቸውን ገልጸዋልል፡፡
እንደነርሱ ሁሉ የውጊያ ልምድ ያላቸው አዋጊዎችና ተዋጊዎች መኖራቸውን የተናገሩት ሚሊሻዎቹ ከጠላት ይልቅ አካባቢውን በሚገባ ስለምናውቀው ጠላትን ቀጥተን እናሸንፋለን ነው ያሉት፡፡
ጠላት በሚያናፍሰው ሐሰተኛ ወሬ ሕዝብ የሚያሸብሩ ሰዎችም እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአማራ ሳይንት ወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋጋው ስሜነው የወረዳው ሚሊሻና አጠቃላይ የታጠቀ ኃይል ጠላትን ለመመከት ወደ ግንባር እንደተንቀሳቀሱ መግለፃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
የአማራ ሳይንት ወረዳ ሚሊሻ የሌሎች ወረዳዎች ሚሊሻዎችን በማደራጀት ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ማድረጉንም አስታውቀዋል።
ሚሊሻው በአጭር ቀን ጠላትን መትቶ አገርንና ሕዝብን ነፃ ለማውጣት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመው በሚሊሻው አደረጃጀት ውስጥ በአገር መከላከያ ሠራዊት ልምድ ያላቸው አዋጊዎችና ተዋጊዎች መኖራቸውንም ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን