Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ከ3 ሺህ 500 በላይ ድርጅቶች ተመዝግበው በሥራ ላይ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከ3 ሺህ 500 በላይ አገር አቀፍና የውጭ አገር ድርጅቶች ተመዝግበው በሥራ ላይ መሆናቸውን የሲቪል ማኅበረሰቦች ድርጅት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጅማ ዲልቦ ለኢፕድ እንደገለፁት ÷ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ3 ሺህ 500 በላይ አገር አቀፍና የውጭ አገር ድርጅቶች ተመዝገበው በሥራ ላይ ናቸው፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው ሁኔታ እነዚህ ድርጅቶች በርካታ ፈተናዎች ተጋርጠውባቸው የቆዩ በመሆናቸው ቁጥራቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ መጥቶ ነበር፡፡

እንደ አቶ ጅማ ገለፃ ÷ ዘርፉ ከዚህ በፊት ይመራበት የነበረው አዋጅ የተዛባ አመለካከት በማኅበረሰብ ውስጥ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

በዚህም ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ተደርጎ ይተረክ ነበር ያሉት ዳይሬክተሩ ÷ ‘‘የውጭውን ዓላማ የማስፈጸሚያ መንገዶች ናቸው’’ ተብሎም ስለሚታሰብ ሴክተሩ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲጫወት እንዳልተደረገ ነው የገለጹት፡፡

ይህንም ታሳቢ በማድረግ በቅርቡ በአዲስ አደረጃጀት እንዲዋቀሩ በመደረጋቸው ድርጅቶቹ የሚሰጡት አገልግሎት መሻሻሉን አንስተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.