የሀገር ውስጥ ዜና

ከፑሽኪን አደባባይ -ጎተራ ማሳለጫ መንገድ ሁለተኛ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተከናወነ ነው

By Feven Bishaw

November 15, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፑሽኪን አደባባይ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ሁለተኛ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ በተባለ የስራ ተቋራጭ እያስገነባው የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክት የመጨረሻው የአስፋልት ንጣፍ ስራ ነው እየተከናወነለት የሚገኘው።