ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያ አንካራ አዲስ ተዋጊ ጄት ለማምረት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

By Feven Bishaw

November 15, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ አንካራ አዲሱን አምስተኛ ትውልድ ተዋጊ ጄት ለማምረት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።

ሞስኮ የኔቶ አባል የሆነችውን ቱርክ አዲሱን ተዋጊ ጄት እንድታመርት ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን የሩሲያ ወታደራዊ-ቴክኒካል ትብብር አገልግሎት ኃላፊ ዲሚትሪ ሹጋዬቭ ተናግረዋል።