Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ጸጥታ ለሚጠብቁ የህብረተብ ክፍሎች ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ አደረጃጀት መስርተው የአካባቢያቸውን ጸጥታ ለሚጠብቁ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል፡፡
በዚህ መሰረት የልደታ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አቃቂ ክፍለ ከተሞች በህዝብ አደረጃጀት ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ጸጥታ ለሚጠብቁ የህብረተብ ክፍሎች ስልጠና መስጠት ጀምረዋል፡፡
ስልጠናው ነዋሪዎች አሸባሪ ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል እና ምሽትን ተገን በማድረግ የሚፈጠሩ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር የጀመሩትን የጸጥታ ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
ስልጠናው በማህበረሰብ ዓቀፍ በጎ ፍቃደኝነት፣ ወንጀልን መከላከልና ስነ ምግባር ላይ እንዲሁም የህዝባዊ ሃይሉ ተልዕኮ ላይ ግልጸኝነት መፍጠር ላይ ያተኮረ መሆኑን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.