ህወሓት በሀረሪ የአብሮነት እሴት እንዲከሰም ይሰራ ነበር- የክልሉ መንግሥት
አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በሐረሪ ክልል ሲያካሂደው በነበረው የከፋፍለህ ግዛ ስልት በህዝቦች መካከል የጠላትነት ስሜት እንዲጎለብትና በብሔር ብሔረሰቦች እና ሀይማኖቶች መካከል የነበረው የመቻቻል፣ የፍቅር፣ የአንድነት እሴቶች እንዲከስም አድርጎ ቆይቷል ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ÷ ባለፉት አመታት አሸባሪው ህወሓት በክልሉ ባካሄደው የከፋፍለህ ግዛ ስልትና የሴራ ፖለቲካ አንዱ ሌላውን ጠልፎ እንዲጥል ሲሰራ ቆይቷል።
በክልሉ ህዝብ መካከል የጠላትነት ስሜት እንዲስፋፋና አንዱን ጠላት ሌላውን ደግሞ ወዳጅ አድርጎ በመፈረጅ በክልሉ በአብሮነት የመኖር እሴት እንዲጠፋ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
በዚህም በተለይ በብሔር ብሔረሰቦች እና ሀይማኖቶች መካከል የነበረው የመቻቻል፣ የፍቅር፣ የአንድነት እሴቶች ሲከስሙ መታየታቸውን ተናግረዋል።
ይህ የከፋፍለህ ግዛ መርህና የሴራ ፖለቲካ ለሐረሪ ክልል ህዝብ ከጠላትነትና ከመገፋፋት ስሜት ያለፈ ጠቀሜታ እንዳላገኘ ነው የጠቆሙት።
ሆኖም ከለውጡ ወዲህ በክልሉ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ሀይማኖቶች በመቻቻል፣ በአብሮነትና በወንድማማችነት አብረው እንዲኖሩ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ እንቅስቃሴ መኖሩንም ነው የገለጹት፡፡
ከብልፅግና ፓርቲ ምስረታ በኋላ ቀደም ሲል የነበረው የሴራና የመጠላለፍ ፖለቲካ በመቅረፍ የወንድማማችነትና በዴሞክራሲያዊ ፖለቲካ ለመቀየር ርብርብ መደረጉን ገልጸዋል።
የአብሮነትና የዴሞክራሲ ፖለቲካ ያልተመቸው አሸባሪው ቡድን ወደ ስልጣን ለመመለስና ቀደም ሲል ሲያራምደው የቆየውን የሴራና የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካ መርህ ለመተግበር ጥረት እያደረገ ቢሆንም ህዝቡ ከዳር ዳር በመነቃነቅ የአሸባሪውን እኩይ አላማ እያከሸፈው ነውም ብለዋል፡፡
የክልሉ ህዝብም በህልውና ዘመቻው ላይ ተጋድሎ እያደረጉ ለሚገኙት የአገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልል ልዩ ሀይሎች የተጠናከረ ድጋፍ በማድረግ ደጀንነቱን እያስመሰከረ ይገኛል መባሉን ከሐረሪ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!