አየር ኃይሉ በኤር ፖሊስ ኮማንዶ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመጀመሪያ ዙር በኤር ፖሊስ ኮማንዶ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ፡፡
በሰራዊታችንና በህዝባችን መስዋዕትነት የተደቀነብን የህልውና አደጋ እየተቀለበሰ ይገኛል ሲሉ የአየር ኃይሉ ምክትል አዛዥ ለአየር ሎጀስቲክስ ብ/ጄ ነገራ ሌሊሳ ተናግረዋል፡፡
አየር ኃይሉ ለምድር ኃይላችን የውጊያ ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ÷ የጠላት ወረዳ ድረስ ዘልቆ በመግባት አሸባሪ ቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ተመራቂ ዎችም ለተቋሙ የግዳጅ አፈፃፀም ስኬታማነት ተጨማሪ አቅም በመሆናችው÷ ለቀጣይ ተልዕኮ እራሳቸውን ሊያዘጋጁ ይገባል ተብሏል፡፡
የስልጠናው አስተባባሪ ኮ/ል ተፈራ እሸቴ በበኩላቸው÷ ሰልጣኞች የሚሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት መወጣት የሚያስችል ስልጠና በመውሰድ በላቀ ውጤት ማጠናቀቅ መቻላቸውን ገልፀዋል።
ተመራቂዎች በሰጡት አስተያየት÷ ስልጠናው ወደ ፊት የሚሰጠንን ማንኛውንም ግዳጅ በፅናትና በቁርጠኝነት እንድንወጣ አጋዥ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!