Fana: At a Speed of Life!

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር 4 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የሚገመት የሰንጋ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በወሎ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦር 4 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የሚገመት የሰንጋ ድጋፍ በመካነ ሰላም ከተማ ተገኝቶ አበረከተ፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ በላይነህ የኔሰው ÷ በወሎ ግንባር ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ በመተከል ዞን ሠላም እያስከበረ ለሚገኘው የወገን ጦር እና በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኙት የወገን ጦሮችም ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ምክትል አስተዳዳሪው ÷ በወሎ ግንባር 116 ሰንጋዎችን ፣ 118 ፍየሎች እና 15 በጎች ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለጹ ሲሆን ድጋፉም 4 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር እንደሚገመት ነው የተናገሩት፡፡

በብሔረሰብ አስተዳደሩ በተለያዩ ግንባሮች የተላከው ድጋፍም በአጠቃላይ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚገመት ነው የገለጹት፡፡

ብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሚሊሻና ወጣቶችን ለዘመቻ መላኩን አስታውሰው ፣ የገባው ዘማችም ጀብዱ እየፈጸመ መሆኑን ነው ያነሱት።

በግንባሩ የአገው ፈረሰኞች ማኅበርም ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የማኅበሩ ሰብሳቢ የሆኑት ጥላዬ አየነው ÷ ትውልዱ አባቶቹ ኢትዮጵያን ሳያስደፍሩ እንዳስረከቡት የአባቶቹን ፈለግ ተከትሎ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ማኅበሩ 600 ሺህ ብር በማሰባሰብ 120 በጎችን ድጋፍ ማድረጉን አስረድተዋል ፤ የስንቅ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈም እንደ ጀግኖች አባቶቹ በውጊያ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

ድጋፉን የተቀበሉት በግንባሩ የአማራ ልዩ ኅይል የሎጅስቲክ አስተባባሪ ሻለቃ አማረ ተሰማ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በተደጋጋሚ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል።

የተደረገው ድጋፍም ለሠራዊቱ ከፍተኛ የሞራል ስንቅ እንደሚሆነው እና ሠራዊቱ ለሚኖረው ግዳጅ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ማለታቸውን የዘገበው አሚኮ ነው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.