በተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጃዊ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ15 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰ ፖሊስ አስታወቀ።
አደጋው የደረሰው ዛሬ ጠዋት ሶስት ሰዓት አካባቢ በወረዳው ሊበን ጋሞ ቀበሌ ውስጥ መሆኑን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ክፍል ሃላፊ ዋና ሳጂን ግዛቸው ዳማ ለኢዜአ ተናግረዋል።
የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-28008(አ.አ) ኤፍ ኤስ አር ተሸከርካሪ ከኢጃጂ ወደ አምቦ 19 ተሳፋሪዎች ጭኖ ሲጓዝ ከነበረው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 6944(ኦሮ) ሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ አደጋው ሊደርስ እንደቻለ ገልጸዋል።
በዚህም የሚኒባሱ አሽከርካሪን ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ የ’ኤፍ ኤስ አር’ አሽከርካሪ እጁን ለፖሊስ መስጠቱን አስታውቀዋል።
ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 15 ሰዎችም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነው ዋና ሳጂን ግዛቸው የገለጹት።
የአደጋው መንስኤና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን አስረድተዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!