Fana: At a Speed of Life!

ማህበራዊ ሚዲያን ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማሰባሰብ እየተጠቀምንበት ነው – ‘የእናት አገር ጥሪ’ ኮሚቴ አባላት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማኅበራዊ ሚዲያን የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ እየተጠቀምንበት ነው ሲሉ ‘የእናት አገር ጥሪ’ ኮሚቴ አባላት ጋዜጠኞች ተናገሩ።

በቅርቡ በአምስት ሴት ጋዜጠኞች ጥምረት የተመሠረተው “የእናት አገር ጥሪ” የጋዜጠኞች ኮሚቴ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ እያዋለው መሆኑን ገልጿል።

በተለይም ደግሞ ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማሰባሰብ እየተጠቀሙበት መሆኑን የኮሚቴው አባላት ጋዜጠኞች ለኢዜአ ተናግረዋል።

የኮሚቴው ሰብሳቢ ጋዜጠኛ ስመኝ ግዛው ለኢዜአ እንዳለችው፥ መከላከያ ሠራዊትን ለማገዝ በተለያዩ ሚዲያ ከሚሰሩ አራት ሴት ጋዜጠኛ ጓደኞቿ ጋር ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግራለች፡፡

ጋዜጠኞቹ ለመጀመሪያ 100 ኩንታል በሶ ለአገር መከላከያ ሠራዊት ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ገልጻ ፥ ድጋፉም በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰባሰበ መሆኑን ጠቁማለች።

የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም በጎ ምላሽ ማሳየታቸውንና ድጋፉን ለማስፋት በኮሚቴው ስም የባንክ አካውንት ተከፍቶ ድገፍ የማሰባሰቡ ጥሪ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጻለች።

እስካሁንም 300 ሺህ ብር ማሰባሰብ መቻሉን ጋዜጠኛ ስመኝ ግዛው ተናግራለች።

ኅብረተሰቡ በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በዓይነትም ድጋፍ ለመስጠት ፍቃደኝነቱን ማሳየቱን ጋዜጠኞቹ ጠቁመዋል።

ጋዜጠኛ አዜብ ታምሩ ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም እየሰራን ያለነው ስራ ሕዝቡ ለሠራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ያስችለዋል ብላለች።

በተለይም ሠራዊቱን ለመደገፍ እድል ያላገኙ ሰዎች እድል እንዲያገኙ እንደሚያስችልም ገልጻለች።

ጋዜጠኛ ሻለቃ የወይንሐረግ በቀለ በበኩሏ፥ ሰራዊቱን ሰዎች በሚችሉት አቅም በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በሞራልና በሌሎችም መንገዶች ማገዝ አለባቸው ትላለች።

ኮሚቴው በማኅበራዊ ሚዲያ በመታገዝ የተለያዩ የድጋፍ ማሰባሰብ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጻ ፥ ስንቅ የማዘጋጀት ተግባርን ያሳለፍነው ቅዳሜ መጀመራቸውን ትናገራለች።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.