Fana: At a Speed of Life!

ከ60 በላይ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከ60 በላይ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ገቢን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ።
በኮሚሽኑ የኤክስፖርት ፕሮጀክቶች ፋሲሊቴሽን ዳይሬክተር ሳሙኤል አሰፋ ÷ ኢትዮጵያ የኤክስፖርት ምርቷን በማስፋት የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት እያደረገች ያለውን ጥረት አብራርተዋል።
በዚህም የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ጨምሮ ከ60 በላይ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ላይ መሆኗን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ወደ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና የተለያዩ የአፍሪካ አገራት እየተላኩ መሆኑን ዳይሬክተሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ የሚመረቱ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን በስፋት በማስተዋወቅ ገበያ እንዲያገኙ ማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ነው አቶ ሳሙኤል የገለጹት።
በተለይም የማዕድን ዘርፉ በታቀደው ልክ ከተሰራበት ኢትዮጵያ ከዘርፉ ከፍ ያለ የውጭ ምንዛሬ ታገኝበታለች ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ በያዘችው የአስር ዓመት የልማት እቅድ በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ሌሎች መስኮች ላይ በማተኮር በየዓመቱ በአማካይ 10 በመቶ እድገት የማስመዝገብ እቅድ እንዳላት ይታወቃል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.