Fana: At a Speed of Life!

ሀሰተኛ መረጃ የህወሓት የውጊያ ስልት በመሆኑ መረጃዎችን በሚገባ መመርመር እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት የአሸባሪው ህወሓት አንዱ የውጊያ ስልት በመሆኑ የሚደርሱንን መረጃዎች በሚገባ መመርመር አለብን ሲሉ የቀድሞ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ገለጹ።
የቀድሞ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር መኮንን የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ሰብስቤ ንጋቱ እና ኮሎኔል ገበየሁ አበበ ለኢዜአ እንደተናገሩት÷ አሸባሪው ህወሓት ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝብን ለማሸበር እየሰራ ይገኛል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨትን አንዱ የውጊያ ስልት አድርጎ እየተጠቀመበት በመሆኑ÷ ትክክለኛ መረጃ በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ሀሰተኛ መረጃዎችን መመከት እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡
ህብረተሰቡ አሸባሪ ቡድኑ በሚያሰራጫቸው መረጃዎች ሳይደናገር የሚደርሱትን መረጃዎች አንጥሮ ሊጠቀም እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡
አንዳንድ የምዕራባውያን ሚዲያዎች ኢትዮጵያን በሚመለከት የሚያሰራጩትን ሀሰተኛ መረጃ ለመመከት የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች የኢትዮጵያን እውነት ተደራሽ ማድረግ እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
በተለይ ምሁራን የተግባቦት አውታሮችን በመጠቀም የአገራቸውን እውነት የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ጨምረው ገልጸዋል።
ኮሎኔል ገበየሁ አበበ በበኩላቸው÷ አንዳንድ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ሆን ብለው የተሳሳቱ ዘገባዎችን እንደሚያሰራጩ መገንዘብ ይገባል ነው ያሉት፡፡ ከዚህ አኳያ ኀብረተሰቡ በየጊዜው በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች መደናገር እንደሌለበትና መረጃን ከትክክለኛ ምንጭ መውሰድ እንዳለበት መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ትስስራቸውንና አንድነታቸውን በማጠናከር ለህልውና ዘመቻው ስኬት መስራት እንዳለባቸውም ነው ያነሱት፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.